የመዲና አማኑኢል ፀበል የኮባው/መዲና/ አማኑኤል ፈዋሽ ጸበልና ጥንታዊ ቤተክርስቲያን በግሼ ወረዳ በጎልታ መዘራዝር ቀበሌ ከራቤል ከተማ በግምት 40 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ይገኛል፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን በግራዝማች መኮንን ዘውዴ አማካኝነት ከፀበሉ ራቅ ብሎ በኮረብታ ላይ ተስርቶ አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ በአፄ ምንሊክ ዘመነ መንግስት ራሳቸው አጼ ሚኒሊክ ጸበሉን ከቦታው ድረስ በመሀድ ከጸበሉ ቅ ካለ ቦታ ተሰርቶ የነበረውን ቤተ ክርስቲያ ከጸበሉ ጎን እንዲሰራ ማድረጋቸውን መረጃውን የሚያቁ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይሕን ፈዋሽ ፀበል በአጼ ዮሀንስ ዘመነ መንግስት መስከረም 11/1800 ዓ/ም በይፋ የታወቀ ሲሆን ከተለያዩ በሽታዎች ፈዋሽ ጸበል በመሆኑ ጎልቶ የታወቀ ነው፡፡ አይነ ስውራንን አብርቷል፣ ከሆድ ውስጥ የተለያዩ ነፍሳትን በማስወጣት፣ ከመንፈስ ናከተለያዩ በሽታዎች በፈዋሽነቱ የታወቀ ነዉ፡፡ ለየት የሚያደርገው መንፈስ ያለበት ሰው ጸበሉን ሲጸበል ድንገት ከጸበሉ ውስጥ ወጥቶ ራቁቱን ድንጋይ ተሸክሞ ቤተክርስቲያኑ ጋር በመሄድ ሶስት ጊዜ ከዞረ በኋላ መንፈሱ ሲለቀው ድንጋዩን ጥሎ ራቁቱን መሆኑን ሲያውቀው በድንጋጤ ልብሱን ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ከወረዳው ጋር የሚያገናኝ የትርንስፖርት አገልግሎት ባይኖረውም እንኳን ከአጎራባች ወረዳዎች በእግራቸዉ ረዥም ጉዞ ተጉዘው በመምጣት በቦታው ላይ እስከ 7 ቀን በመቆየት ከበሽታ ተፈውሰው ይማህበረሰብ በጋራ በመሆን 75 ቆርቆሮ ለፀበልተኛ ማረፊያ ቤት ቦታው ላይ ተሰርቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡ ግንቦት 28 የቅዱስ አማኑኤል አመታዊ ክብረ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች በርካታ ምዕመናን ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ የሚሆንበትና በአሉ የሚከበርበት ነው፡፡ በመሆኑም የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤትእና የአካባቢው ማህበረሰብ በዓሉ በድምቀት ያከብራል
Just another WordPress site