
በዚህም መሰረት ለደመወዝ 166 ሚሊዮን 747 ሺ 472 ብር፤ ለካፒታል በጀት 6 ሚሊዮን 241ሺ 675 ፤ ለስራ ማስኬጃ 30 ሚሊዮን 435ሺ 800 ብር፤ የውስጥ ገቢ 6 ሚሊዮን 120ሺ 865 ብር፤ ከእርዳታ 109 ሺ 265 ብር፤ በድምሩ 209 ሚሊዮን 655 ሺ 80 ብር የ2015 በጀት አመት አጠቃላይ በጀት ሆኖ ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን የምክር ቤት አባሉም በጀቱ ለታለመለት አላማ በአግባቡ እየተመራ ተግባር ላይ እንዲውልና የህዝብን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ የሚችል ስራ መሰራት እንዳለበት አስተያየት በመስጠት በጀቱን አጽድቋል፡፡