የግሼ ወረዳ መስህብ ቦታዎች

ስለ ታላቁ አጼ ዋሻ

አካባቢያችንን እና ሀብቶቻችንን እንወቅ እናሳውቅ

አጼ ዋሻ በግሼ ወረዳ ልዩ ስሙ የሻ በሚባል ስፍራ ይገኛል። ወደ አጼ ዋሻ የሚደረገው ጉዞ በዳገትና ቁልቁለት የታጀበ ሲሆን በሁለት አቅጣጫዎች ወደ ዋሻው መድረስ ያቻላል፡፡ አንደኛው አቅጣጫ በመኪና እስከ ግራር አምባ ከተማ ድረስ ከዚያም በእግር እስከ ዋሻው መጓዝ፤ ሁለተኛው ከራቤል ከተማ በእግር ጉዞ በዳራት አቦ ወርደው ወንዙን በመሻገር ዋሻው በር ላይ መድረስ ይቻላል፡፡

አጼ ዋሻ ግሼ ወረዳን ከሁለት የሚከፍለው ትልቁ የቄጤማ ወንዝ ከጀርባው አጋድሞ ግርማ ሞገስን ተላብሶና በኩራት ደረቱን ገልብጦ የሚታየው ይህ መጀመሪያው እንጂ መጨረሻው የማይታወቅ ዋሻ የታሪክ እማኝነቱን ለመናገር የፈለገ ይመስል፤ ከኮረብቲት ቀበሌ በኩል ሆኖ ለተመለከተው በስፋት አፉን ከፍቶ ሲያዩት አንዳች ስሜት መላ ሰውነትን ይወርራል። ጀግናው ብሩኬ ደምሴ በፅናት የተዋጋባቸው የየሻ ሰንሰለታማ ተራሮችን ተከቦ የሚገኘው አጼ ዋሻ ተፈጥሯዊ አቀማመጡና ዙሪያ ገባው አንዳች ምትሃታዊ ተፈጥሮነት አለው።

አጼ ዋሻ ከመስህብነቱም ባለፈ በመሆን ለክፉ ቀን ምሽግ እና ከለላ በመሆን በአርበኛነት ያገለገለ ሲሆን ለዚህም በ1960ቹ አካባቢ ጀግናው ብሩኬ ደምሴ እና የራስ ብሩ ልጆች ማለትም መርዕድ ብሩና መስፍን ብሩ ደርግን በጀግንነት ተፋልመውበታል፡፡

ይህን ዋሻ አፄ አምደ ፂዎን ገብረ መስቀል ስመ መንግስቱ ገብረ መስቀል ከ1314-1344 ዓ.ም ድረስ በገዙበት ዘመን ይህንን የአፄ ዋሻ ቦታው ድረስ ሄደው ያዩት ሲሆን በ1316 ዓ.ም የአካባቢውን ህዝብ ሰብስበው የዋሻው ውስጣዊ ክፍል እንዲፀዳ አድርገዋል፡፡ ይህን ያደረጉበት ዋናው ምክንያት ከ857-987 ዓ.ም ድረስ ዩዲት ጉዲት በኢትዮጵያ አብያተ- ክርስቲያናትና በንዋየ ቅዱሳቱ ላይ የፈፀመችውን የማይሽር ጠባሳ ያውቁ ስለነበር ምናልባትም የእርሷ አይነት የሀገር አጥፊዎች ቢነሱ እንኳን በወቅቱ ግሼ ያስተዳድራቸው የነበሩትን የአብያተ-ክርስቲያናት ንዋየ ቅዱሳትን ለማስቀመጫነት አስበው እንደነበር መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

ይህንን ውብ፤ አስደናቂና ታሪካዊ ዋሻ እንጎብኝ መልእክቴ ነው

ሰላም

About the Great Emperor’s Cave

Let’s know our environment and resources.

Emperor cave is found in a place called Yesha in Gishe district. The journey to the Emperor’s Cave is paved with hills and depths and you can reach the cave in two directions. The first direction is by car to Girar Amba city and then by foot to the cave; the second one is from Rabel city by walking down Darat Abo and crossing the river to the cave gate.

Emperor Cave Gishe Woreda, the river Ketema, which divides the district in two, is dressed in grace and proud, as if this cave with no end, is trying to tell his true faith in history. When you see it from Korrebitit Kebele, you will get a feeling when you see it. The natural location of the Emperor Cave which is surrounded by Yesha Senseltama mountains that the hero Biruke Demissie fought with persistence has a magical nature.

Emperor Cave was not only his attraction but also a shelter for bad times and served as a patriot. That is why in 1960 the hero Biruk Demissie and the children of Ras Birru, Mered Bruna and Mesfin Birru fought heroically against Dergue.

This cave was named after Emperor Amdesiwon Gebre Meskel from 1314-1344 E.C. They went to see this Emperor’s cave in 1316 E.C. They gathered the people of the area to clean the cave. The main reason for this is from 857-987 E.C. Yudit Gudit knew the scar that she did on Ethiopian churches and Nwaye Kidusatu, so the evidence shows that she was planning to keep the churches that she managed at the time.

Let’s visit this beautiful, amazing and historic cave. It is my message.

የመዲና አማኑኢል ፀበል የኮባው/መዲና/ አማኑኤል ፈዋሽ ጸበልና ጥንታዊ ቤተክርስቲያን በግሼ ወረዳ በጎልታ መዘራዝር ቀበሌ ከራቤል ከተማ በግምት 40 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ይገኛል፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን በግራዝማች መኮንን ዘውዴ አማካኝነት ከፀበሉ ራቅ ብሎ በኮረብታ ላይ ተስርቶ አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ በአፄ ምንሊክ ዘመነ መንግስት ራሳቸው አጼ ሚኒሊክ ጸበሉን ከቦታው ድረስ በመሀድ ከጸበሉ ቅ ካለ ቦታ ተሰርቶ የነበረውን ቤተ ክርስቲያ ከጸበሉ ጎን እንዲሰራ ማድረጋቸውን መረጃውን የሚያቁ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይሕን ፈዋሽ ፀበል በአጼ ዮሀንስ ዘመነ መንግስት መስከረም 11/1800 ዓ/ም በይፋ የታወቀ ሲሆን ከተለያዩ በሽታዎች ፈዋሽ ጸበል በመሆኑ ጎልቶ የታወቀ ነው፡፡ አይነ ስውራንን አብርቷል፣ ከሆድ ውስጥ የተለያዩ ነፍሳትን በማስወጣት፣ ከመንፈስ ናከተለያዩ በሽታዎች በፈዋሽነቱ የታወቀ ነዉ፡፡ ለየት የሚያደርገው መንፈስ ያለበት ሰው ጸበሉን ሲጸበል ድንገት ከጸበሉ ውስጥ ወጥቶ ራቁቱን ድንጋይ ተሸክሞ ቤተክርስቲያኑ ጋር በመሄድ ሶስት ጊዜ ከዞረ በኋላ መንፈሱ ሲለቀው ድንጋዩን ጥሎ ራቁቱን መሆኑን ሲያውቀው በድንጋጤ ልብሱን ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ከወረዳው ጋር የሚያገናኝ የትርንስፖርት አገልግሎት ባይኖረውም እንኳን ከአጎራባች ወረዳዎች በእግራቸዉ ረዥም ጉዞ ተጉዘው በመምጣት በቦታው ላይ እስከ 7 ቀን በመቆየት ከበሽታ ተፈውሰው ይማህበረሰብ በጋራ በመሆን 75 ቆርቆሮ ለፀበልተኛ ማረፊያ ቤት ቦታው ላይ ተሰርቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡ ግንቦት 28 የቅዱስ አማኑኤል አመታዊ ክብረ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች በርካታ ምዕመናን ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ የሚሆንበትና በአሉ የሚከበርበት ነው፡፡ በመሆኑም የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤትእና የአካባቢው ማህበረሰብ በዓሉ በድምቀት ያከብራል