ስለኛ

የአስተዳደር ጽ/ቤት ራዕይ፤ተልዕኮና እሴቶች

             የጽ/ቤቱ ተልዕኮ፡-

ለአስተዳድር ም/ቤቱ ደረጃውን የጠበቀና ህገ መንግስታዊ ሀላፊነቱን በብቃት መወጣት የሚያችለውን ሁለገብ ድጋፍ በመስጠትና የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለውና ወጤታማናቱ በተረጋገጠ መንገድ በማከናወን፤ የበላይ አመራሩ ከሚያስተባብራቸው ዞን  አቀፍ አስፈጻሚ መስሪያቤችና በተዋረደ ከሚቆጣጠራቸው የየእርከኑ አስተዳደር አካላት ጋር ያሉት ግንኙነቶች እንዲሳለጡ፤ በህግ የበላይነት አስተሳሰብ ላይ ተመስርተው እንዲፈጸሙ በበላይና በበታች የመንግስት አካላት መካከል ግልጽ የሆነና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር እርአት ማስፈን።

     የጽ/ቤቱ ራዕይ፡-

ህ/ሰቡ በአገልግሎት አሰጣጣችን እረክቶ በክልሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያወጣቸው ህጎች የወረዳውን የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ችግሮችን በ2015 ዓ.ም ተፈትተው ሰላም ደሞክራዊና ልማት የሰፈነበት ወረዳ ተፈጥሮ ማየት

የጽ/ቤቱ እሴቶችና የሥራ መርሆዎች

ጽ/ቤቱ የሚያቅዳቸውን እቅዶች በተሟላ መልኩ ለመፈፀም የሚከተላቸው የሥራ መርሆዎችና እሴቶች የሚከተሉት ናቸው፦

  • በየደረጃው ብቃት ያለው አመራር እንዲፈጠር የምናደርገውን ድጋፍ  አጠናክረን አንቀጥላለን፣
  • ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን በስራ እናረጋግጣለን፣
  • ፍትሃዊ የሆነ ህግ እንዲወጣና ተግባራዊ እንዲሆን እንሠራለን፣
  • የህግ የበላይነትን እናከብራለን፣
  • የባለጉዳዮቻችንን ጥያቄ በጥሞናና በትህትና እናዳምጣለን፣ በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን፣
  • በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የሥርዓተ ጾታ መርህን እንከተላለን፣
  • የሕብረተሰቡንና የመ/ቤቱን ሠራተኞች ዲሞክራሲያዊ ተሣትፎ ያረጋገጠ የአሰራር  ስርአት እንከተላለን፣
  • የግለሰቦችን ጥረትና ተነሳሽነት እንዲጎለብት ጠንክረን እንሠራለን፣
  • ተደጋግፎ የመስራት ባህልና መተማመን በመ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰፍን እናደርጋለን።
  • የግለሰብና የቡድን መብትን እናከብራለን፣