Get Adobe Flash player
Gishe In Pictures
LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5
user log in

ዳየር ማርያም

የዳየር ማርያም ከራቤል ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል በፈ/ቤት ቀበሌ በግምት 15 .ሜትር ያህል ከተጓዙ በኋላ የምትገኝ በአንድ የመስቀል ቅርጽ ባለው ኮረብታ ላይ የተመሰረተችና ዙሪያዋን ቀጥ ባለ ገደል የታጠረች ጥንታዊ ቤተ-ክርስቲያን ስትሆን በቁጥቋጦ ደን የተሸፈነችና ከአካባቢው መልከአምድራዊ አቀማመጥ ሲታይ በሚያስገርም ሁኔታ ከፍተኛ ቦታ መሆኗ ሁል ጊዜ ንፁህ አየር መፍለቂያና በጣም የደስ ደስ ያላት ስፍራ አድርጓታል ፡፡ ዳየር ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ከታጠረችበት ትልልቅ ገደል ጫፍ ላይ ሆኖ አካባቢውን ቁልቁል ሲመለከቱ ከአየር ሆነው የመሬትን ክፍል የሚጐበኙ እስከሚመስል ድረስ ሰንሰለታማ ገደሎች ሸለቆዎች፣ ዙሪያውን የሚፈሱ ወንዞች የቁጥቋጦ ደኖች ወፎች ስለሚታዩ የተመለካችን ልብ በሐሴት ይሞላል ፡፡ ይህቺ ታሪካዊና ጥንታዊ ልዩ የሆነ የቦታ አቀማመጥ ያላት የዳየር ማርያም ቤተ-ክርስቲያን 7ዐዐ . በፊት ተመስርታ መስዋዕተ ኦሪት ይሰዋባት የነበረ ሲሆን ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ 17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ዳኤሮ የተባሉ ቄስ በጐንደሪያን ዘመን ማለትም 1732 . በፋሲለደስ አገዛዝ ታቦተ ህጉን ከጐንደር ይዘው መጥተው እንዳስገቡና ከእርሣቸው ዳኤሮ ከሚለው ስም ተወስዶ ዳየር እንደተባለ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ መቤተ-ክርስቲያኗ ውስጥ በግድግዳ ላይ በግልጽ ተፅፎ የሚታው የግዕዝ ፅሁፍ ስለ ቤተ-ክርስቲያኗ አመሰራረት እንድህ ይላል ንፅሕፍ ለኩሙ ዘከመ ተሐንፁት ዛቲ ቤተ-ክርስቲያን ወተሥዕለት ኪነ ወጣኒ ­ህንፃሐ +0 40% 7 . በታስዕ ህመተ መንግስቱ ለንጉስኒ ዩሐንስ ወፍፃሜሃኒ +0 40 . % 2 ዓመተ መንግስተ ተስዕሎታኒ ተወጥኒ +0 4 ዓመተ አለም በሳብዕ ዓመተ መንግስተ ለንጉሳኒ እያሱ ወበፀጋ እንግዚአብሄር ተስመየ አድያም ሰገድ ወከነ ፍፃሜሁ በውእቱ ዓመት በረድኤተ እግዚአብሄር ፡፡ በዚህም መሰረት ቤተ-ክርስቲያኗ 7ዐዐ . በፊት ለመመስረቷ አያጠራጥርም፡፡

በወቅቱ ከፃድቃኔ ማርያም ቀጥሎ የምትታወቀው ዳየር ማርያም የነበረች ሲሆን የተለያዩ ነገስታት ቦታውን ጐብኝተውታል ፡፡ ከእነዚህም መካከል ልብነ-ድንግል ህዝቅያስ ዘርአያዕቆብ ናአድና /ስላሴ ናቸው ፡፡ አፄ /ስላሴ አሁን ያለው የቤተ-ክርስቲያኗ የጣሪያ ቆርቆሮ ከመቀየሩ በፊት የነበረው የክዳን ቆርቆሮ በቀጥታ እርሣቸው ሰጥተው አስርተውት ነበር ፡፡ በዚችው ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ አንድ በጣት የምትነሣ ከባድ ቀለበት መሳይ ታሪካዊ እቃ ከአፄ ዘርአያዕቆብ የተሰጠች መሆኑን አባቶች ይናገራሉ ፡፡

በቤተ-ክርስቲያኗ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ አስደናቂ ነገሮች

Ø መጥምቁ ዩሃንስ ይለብሰው የነበረ ከግመል ፀጉር የተሰራ ልብስ

Ø 17ኛው /ዘመን የተሣሉና የተፃፉ የግድግዳ ላይ ስዕላትና ልዩ ልዩ ፅሁፎች

Ø በጣት የምትነሣ ታሪካዊ ቀለበት

Ø ከዘርአያዕቆብ የተሰጡ ልዩ ልዩ መስቀሎችና አልባሳት

Ø አፄ እያሱ የቀደሱበት ልብስ

Ø የዲሜጥሮስ ስም የተፃፈባቸው የተለያዩ ንዋየ ቅዱሳት

በቤተ-ክርስቲያኗ አካባቢ የሚገኙ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ነገሮች

v አፄ ዘርአያቆብ የተከሏቸው 6 ትልልቅ የፅድ ዛፎች

v ጠጅነሽ የምትባል በጠጅ ያደገች ፅድ

v የህግ ታራሚዎች ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው ይታሰሩበት የነበረ የገደል ውስጥ እስር ቤት

v የዲሜጥሮስ ቤተ-መንግስት

v የአካባቢው መስቀለኛ የቦታ አቀማመጥ

v ታሪካዊ የአብሎ ፈራጅ ድንጋይ

ዳየር ማርያም ከደረሱ ሁለት የማይነጣጠሉ የተመልካችን ስሜት የሚሰርቁ መስህቦች ሳይመለከቱ አይመለሱም ፡፡ የመጀመሪያው መስህብ የተላበሰ ቦታ የዲሜጥሮስ ቤተ-መንግስት ፍርስራሽ ነው ፡፡ ይህ ቤተ-መንግስት 17ኛው መቶ /ዘመን አፄ ዲሜጥሮስ የተባለ ንጉስ ሰርቶ አሁን ወረዳና ዞን ተብለው የተከፈሉትን የሰሜን ሽዋንና የደቡብ ወሎ ዞኖችን ያስተዳድር እንደነበር የተያዩ የፅሁፍና የቃል ምንጮች ያወሳሉ ፡፡ እንዲህ እንደ ዛሬው ስልጣኔ ባልሰፈነበት ዘመን ቤተ-መንግስቱ በጭቃና በድንጋይ ለጠላት በማይመች መንገድ የተሰራው ይህ ቤተ-መንግስት ከጊዜ ቆይታ ብዛት ቢፈርስም አብዛኛው ግን አሁንም ድረስ በሚያስገርም ሁኔታ ህያው ሆኖ ይገኛል ፡፡ በተጨማሪም በዘመኑ ምንም አይነት ስልጣኔ ያልነበረና አፄ ዲሜጥሮስ በእርግጥም ንጉስ በነበረበት ወቅት በርካታ ህዝብ ያስተዱድር እንደነበርና አጥፊዎችንም ይቀጣ እንደነበር የሚመሰክር የገደል ውስጥ እስር ቤት በአካባቢው ይገኛል ፡፡ ይህ እስር ቤት በአንድ በኩል ብቻ መግቢያና መውጫ በር ያለውና በዚህ በአንድ በር እስረኞችን አስገብቶ በሩ አካባቢ ጥበቃዎችን በማስቀመጥ እስረኞች የቅጣት ጊዜያቸውን እስከሚጨርሱ ድረስ በዚሁ በገደል ውስጥ ይቆዩ እንደነበር ይነገራል ፡፡ ሌላውና ቀልብ የሚስበው ቦታ የአብሎ ፈራጅ ድንጋይ ሲሆን ከራቤል ከተማ ወደ ዳየር ማርያም ሲሄዱ 1 .ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ቦታ ነው ፡፡ ይህ ድርጊቱ ሲፈፀም ዘመኑ በውል የማይታወቅ ታሪካዊ ድንጋይ ታሪኩ ሲወርድ ሲዋረድ መጥቶ በአሁኑ ሰአት እንደሚነገረው በጥንት ዘመን በካባቢው የነበረ አንድ ዳኛ ከሳሽና ተከሳሽን ግራና ቀኝ አቁሞ እማኝ ሲያሰማ/ሲያስመሰክር/መስካሪዋ ሴት ያላየችውንና ያልሰማችውን ነገር በሀሰት አይቻለሁ ብላ በአድሎ ዋሽታ ስትመሰክር በድንገት እየተናገረች ያለውን እንኳን ሳትጨርስ የተቀመጠችበት መለስተኛ ድንጋይ ተሰጥንቆ በስንጥቁ ውስጥ ሴትዩዋ ሰጥማ እንደቀረች ይነገራል ፡፡ ዛሬም ቢሆን በዚህ አካባቢ የሚያልፍ መንገደኛ ሁሉ በዚች ድንጋይ ላይ በጀርባው ተኝቶ በፍጥነት ከተነሣ ኃጢያት/ወንጀል/ እንደሌለበት ይታመናል ፡፡ በሆኑም አብሎ ማለት ማበል/መዋሸት እንደሆነ ይነገራል ፡፡ ማየት ማመን ነውና ሄደው ይሞክሩ ፡፡ በፍፀም እግርዎን ሳያንቀሳቅሱ መነሳት አይችሉም ፡፡

በአጠቃላይ በዳየር ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ዙሪያ አስደሳችና እጅግ ማራኪ የሆኑ የተለያዩ አይነት ጥንታዊና ተአምራዊ መስህቦች የሚገኙ ሲሆን በግቢው ውስጥ ደግሞ እጅግ ትላልቅ የወይራና የፅድ ዛፎች ቤተ-ክርስቲያኗ ቀደምት ለመሆኗ አብይ ማስረጃዎች ናቸው ፡፡ በዚህ ቦታ እድልና አጋጣሚውን አግኝቶ የደረሰ ሰው ከቦታው ተፈጥሮአዊ ውበትና ኃይማኖታዊ ጠቀሜታ ባሻገር የአካባቢውን መልከአምድራዊ የመስቀል ቅርፅ አቀማመጥና ውበት አይንን የሚማርክና ሃሴትን የሚጭር ነው ፡፡ በመሆኑም ይህንን ተአምር ማየት የሚፈልግ በማንኛውም ጊዜ ወደ ስፍራው መጓዝ የሚችል ሲሆን ህዳር 21 ቀን አመታዊ ክብረ በአሏ ስለሆነ በዚህ ጊዜ መሄድ ተመራጭ ነው፡፡

 

 

Last Updated (Saturday, 31 January 2015 17:26)

 
search
vote
ያለዎት አስተያየት
 
whosonline
We have 3 guests online